"ወጣቶች በሰላም ዕሴት ግንባታው እና በብልፅግና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"ወጣቶች በሰላም ዕሴት ግንባታው እና በብልፅግናችን ስኬታማ ጉዞ ላይ ያላቸው ሚና የጎላ ነው!" አቶ አለማየሁ እጅጉ

ለሰላም ባህል እና አመለካከት ግንባታ የወጣቶች ሚና!' በሚል ርዕስ ከተማ አቀፍ ምክክር መድረክ ከተፅዕኖ ፈጣሪ ወጣቶች ጋር ተካሂዷል። 

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ሊግ የተዘጋጀው ይህ መድረክ በክ/ከተማ እና በወረዳዎች በየደረጃው ሲካሄድ የነበረው "ለሰላም ባህል እና አመለካከት ግንባታው የወጣቶች ሚና!" በሚል ርዕስ ሲካሄድ የነበረው መድረክ ማጠቃለያ ሲሆን ፤ በየደረጃው ያለው የወጣት ሊግ አባላትም ተሳትፈውበታል።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለተገኙ ለውጦች የወጣቶች አበርክቶ የጎላ መሆኑን የጠቀሱት በውይይቱ ላይ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ የከተማዋ ወጣቶች ሰላምን በማስጠበቅ ሂደት ትልቅ አስተዋጽዎ እንደነበራቸዉ ተናግረው እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎችም ጉልህ ሚና እየተጫወቱም ነዉ ፤ በቀጣይም በክረምት በጎ ፍቃድ እንቅስቃሴ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።  

ወጣቶች በከተማችን እና አልፎም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩ የሰላም እና የልማት ስራዎችን ግንባር ቀደም ተተሳታፊ በመሆን ሲሰሩ ቆይተዋል፣ በዚህም የብልፅግና ጉዞዋችንን እውን ለማድረግ የነበራቸው ተሳትፎ እና ውጤታማ ስራ ተምሳሌት የሚሆን ነበር ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በቀጣይም ከዚህ ቀደም ሲያረጉት የነበረውን ስራ በማጠናከር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ውጤታማ ስራዎችን ማስቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ወጣቶች ለከተማችን ሰላም እና ለሀገር ብልፅግና ስኬት እያደረጉት አስተዋፅኦ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ያሉት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት የወጣት ሊግ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት መለሰ አባተ ለሀገረ መንግስት ግንባታው ስኬታማነት የሰላም ዕሴት ግንባታችን ላይ ግንባር ቀደም በመሆን የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሊጉ ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ ወጣት በቀለ ታጀበ በበኩላቸው በከተማው እና አልፎም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተመዘገቡ ድሎች የወጣቶች ሚና የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፣ ይህንን ተግባር በማስቀጠልም የሀገር ግንባታውን እውን የማድረግ ሀላፊነት ይኖርብናል፣ በየደረጃው ካደረግናቸው የውይይት መድረኮች ያገኘናቸውን ተደማሪ አቅም ወደ ውጤት በመቀየር የሰላም አርበኞች መሆን ይጠበቅብናል ነው ያሉት።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.