በርካታ የመሰረተ ልማት ንብረቶች የኤሌክትሪክ እና የቴሌ ኬብሎች በህዝብ ጥቆማ መያዙ ተገለፀ።
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አስተዳደር የመርካቶ አከባቢ ነባር ቀበሌ 22/7 እና 23 ልዩ ቦታው ጭድ ተራ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከህዝብ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ባደረግነው ጥናት በርካታ የመሰረተ ልማት ንብረቶች የኤሌክትሪክ እና የቴሌ ኬብሎች ከነ ተጠርጣሪዎቹ መያዝ ተችሏል። የክፍለ ከተማች ፖሊስ መምሪያ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ምርምራ እያደረገ ይገኛል።
የክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡ የሀገርን እንዲሁም የህዝብ ሀብቶችን በንቃት መጠበቅ እንዳለበት እና ጥፋተኞችን ወደ ሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ እንዳለበት በመግለጽ አሁንም ህብረተሰቡን በማመስገን የተለመደው ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.