6 ሺህ 500 በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የክረም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

6 ሺህ 500 በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉበት የክረምት የትራፊክ አገልግሎት ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በ130 ዓደባባዮች 6 ሺህ 500 በጎ ፈቃደኞች የሚሰማሩበት የክረምት የትራፊክ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

አገልግሎቱን በይፋ ያስጀመሩት ኮሚሽነር አብርሀም ታደሰ አዲስ አበባ ከተማን የበጎ ፈቃደኞች ከተማ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ በጎ ፈቃደኞች እያደረጉት ያለውን የነቃ ተሳትፎ የበጎነት ስነ ምግባሮችን ተላብሰው እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል። 

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለከተማችን ሁለንተናው ብልጽግና የጎላ ሚና አለው ያሉት ኮሚሽነሩ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 15 ፕሮግራሞች የተካተቱበት መርሀ ግብር እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በከንቲባ አዳነች አቤቤ በወርሀ ግንቦት ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ በሌሎች መርሀ-ግብሮች በልበ ቀና በጎ ፈቃደኞች ለበርካታ ወገኖች ህይወት መቃናት ምክንያት የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን ቤተሰብ እንዲሆኑ እንጋብዛለን! አጋርነትዎን የበጎነትና የህብረተሰብ ተሳትፎ ግቦቻችን በመደገፍ ወይም ገንቢ አስተያየትዎን በመለገስ ያረጋግጡ!!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.