"የማንተገብረውን ቃል አንገባም ፤ ቃል የገባነው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

"የማንተገብረውን ቃል አንገባም ፤ ቃል የገባነውን እንተገብራለን!"

ከሜክሲኮ እስከ ሳርቤት ያለው የኮሪደር ልማት ስራችንን አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግመናል:: ከጥቂት የእርማት ስራዎች በስተቀር የተጠናቀቀ ሌላኛው የኮሪደር ልማት ስራች መሆንም ችሏል::

የኮሪደር ልማት ስራችን ትልቅ የመፈጸም ብቃት የታየበት ፣ ለየት ያለ የስራ ባህል የተተገበረበት ፣ ትብብር እና የመሰረተ ልማት ቅንጅት የተሻሻለበት ፣ በርካታ በከተማችን ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ የመሰረተ ልማት አገልግሎት እና ስታንዳርዶችን በአይነት ፣ በጥራት እና በውበት ለከተማችን ያስተዋወቅንበት 

ለከተማችንና ለሃገራችን ትልቅ ብስራት ነው:: 

የከተማዋን ስታንዳርድ ለማስጠበቅ እና ለእግረኛ መተላለፊያነት እንዲውል ህንጻችሁን በማፍረስ እና በሰጠናችሁ ስታንዳርድ መሰረት እድሳት ያደረጋችሁ ተቋማት፣ የቤትና ህንጻ ባለቤቶችእንዲሁም በተለያየ መንገድ በስራው ላይ ለተሳተፋችሁ እና ለተባበራችሁ አካላት ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ::

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች መንገዶቹን በምንሰራባቸው ጊዜያት ለነበረው የትራፊክ መጨናነቅ እና ለተፈጠሩ መጠነኛ ውጣውረዶች ቅር ሳትሰኙ ላሳያችሁን ትዕግስትና ማበረታቻ ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ:: 

ይህንን እና ሌሎቹንም ኮሪደሮች በቀሪ ጊዜያት ውስጥ አጠናቅቀን ለህዝባችንን አገልግሎት እንዲውሉ የምናደርግ ይሆናል:: 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.