ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ወሰን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በዛሬው ዕለት ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ለተመደቡ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአዲስ አበባ የሰላም ሠራዊት ጋር በማስተሳሰር ለአንድ ወር የሚቆይ የክረምት በጎ ፈቃደ አገልግሎት ተጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደተናገሩት ለአንድ ወር የሚቆየዉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትኩረት አድርጎ የሚሰራዉ በማህበራዊ ትስስር፤በልማት ሰራዎች እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ነው ብለዋል፡፡ 

ሀላፊዋ አክለውም ከአዲስ አበባ የሠላም ሰራዊት ጋር በማስተሳሰር ከማእከል እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ ባሉ አደረጃጀቶች ጋር ይሰራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የኢፌዲሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዕታ ዶ/ር ኬይረዲን ተዘራ በመርኃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ሚንስተር መ/ቤቱ ወጣቶችን ትኩረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ከመላዉ ሀገሪቱ የሚገኙ የ2ኛ እና የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ያሰባሰበ ወሠን ተሻጋሪ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ፕሮግራም ቀርፆ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልፅው ይህም ተግባር ለሀገር ግንባታ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።

በመጨረሻም የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ተማሪዎች ይህ ታላቅ ተግባር በብዙሃነታችን አብሮነታችንን አጠናክረን ኢትዪጵያንና ኢትዪጵያዊነትን በማጉላት ጠንካራ ሃገረ-መንግስት ለመገንባት ሚናችን ከፍተኛ ነዉ በማለት ምስጋናቸዉን ጭምር አቅርበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.