ከሁሉ በላይ ድካማችንን ወደ ውጤት የቀየረልን ፈ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከሁሉ በላይ ድካማችንን ወደ ውጤት የቀየረልን ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ፒያሳ - አራት ኪሎ ኮሪደርን ለሥራ ክፍት ባደረግን ሁለተኛ ሳምንት ላይ ሜክሲኮ ሳርቤትንም እነሆ ! 

የኮሪደር ልማት ስራችን 24/7 በመስራት ቃላችንን የጠበቅንበት ፣ የከተማችንን ጎስቋላ ገጽታ የቀየርንበት ፣ ጥራት ፣ ንፅህናን እና ውበት ያዋሃድንበት ፣ ተኪ ምርቶችን በሃገር ውስጥ በማምረት የውጭ ምንዛሪ ያስቀረንበት እንዲሁም አዳዲስ ስታንዳርዶችን ለሃገራችን ያስተዋወቅንበት ነው::

ውድ የከተማችን ነዋሪዎች ቃላችንን የምንጠብቀው ጉስቁልናን እያራገፍን ብልፅግናን ማረጋገጥ ለሀገራችን የሚገባ በመሆኑ ነው። አሁንም ደግመን የምናረጋግጥላችሁ ፤ በእርካታ ሳይሆን በማያቋርጥ የተግባር መንገድ ላይ የምንገኝ መሆኑን ነው።  

በቀጣዩ ሂደታችንም የእውነት፣ የፅናት፣ የትጋት መንገዶቻችንን መገንባታችንን እንቀጥላለን!!

አርቆ በማሰብ ፤ ለየት አድርጎ በማቀድ እንዲሁም በመፍጠንና በመፍጠር መርህ እንድንመራ እንዲሁም በተከታታይ ውጤት እንድናስመዘግብ የመሩን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ከልብ እናመሰግናለን።

በዚህ ሂደት ያስተባበራችሁ፣ የተሳተፈችሁ፣ ሌት ከቀን በትጋት የሰራችሁ፣ በፅናት የቆማችሁ፣ ከፊታችን የዘረጋነው እውነት እና ብልፅግና የታያችሁ አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ከሁሉ በላይ ያገዛችሁን እና የታገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች አመሰግናችኋለሁ!

ቀሪ ኮሪደሮችን በአጭር ጊዜያት ውስጥ አጠናቅቀን በውጤት እየካስናችሁ እንቀጥላለን !!:: 

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.