ዛሬ የከተማችን ልሳን የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትወ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የከተማችን ልሳን የሆነው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአዲስ መልክ እራሱን በማደራጀት ያስጀመረው የአዲስ ቻናል ፣ የብራንዲንግ ስራ እና የታለንት ነው ይፋ አድርገናል::

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማችን ነዋሪዎች አይንና ጆሮ በመሆን ለውጥ በማምጣት ፣ መረጃን በመስጠት፣ በማስተማር እና በማዝናናት ሂደት ውስጥ የራሱን አውንታዊ ሚና እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን የብዝሃነትና የትውልድ ድምፅ መሆኑን በተግባር አሳይቷል::

የከተማችን ነዋሪዎች ሚዲያው የእናንተ መሆኑን በመገንዝብ የትውልድና የብዝሃነት ድምፅ በሆነው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ድምፃችሁን የምታሰሙበት ፣ ትክክለኛ የመረጃ ምንጫችሁ አድርጋችሁ የምትገለገሉበት ፣ ኢፍትሃዊነትን የምትታገሉበት እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ከተማችሁን የምታስተዋውቁበት እንዲሆን ጥሪየን አቀርባለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.