
በመተባበር ከተማችንን እና ሃገራችንን እንገነባለን!ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባን እያስዋቡ እና እያደሱ እንደ አዲስ እየገነቧት ያሉ ብርቱ እጆች እና ጠንካራ ሰራተኞችን በ24/7 የስራ መርሃ ግብር ውስጥ እየተዘዋወርን ይህንን አርሙ፣ አስተካክሉ፣ ፍጠኑ ብሎ መናገር እና ስራን መገምገም ብቻ ሳይሆን ያልተለመደውን የሌሊት ሺፍት ስራ የሚያከናውኑ ሰራተኞችን እራት እንዲበሉና በስራቸው ይበልጥ ተነሳሽ እንዲሆኑ እያመሰገንን እና እያበረታታን እንገኛለን።
በዚህ ፕሮጀክት እየተጉ የሚገኙ ሰራተኞችን በመመገብ እና በማበረታታት ላይ የምትገኙ የከተማችን ነዋሪዎችን በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እንወዳለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.