የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስፋት እና ይዘት አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ነው!
በኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ከተሰሩት መካከል:-
1. የመንገድ መሰረተ ልማቶች
• ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ መንገድ፣
• ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ ሰፋፊ የእግረኛ መንገድ በግራና በቀኝ ተሰርቷል
• 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣
• 4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ (underpass) መንገዶች፣
• 5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣
• 2 ትልልቅ የተሽከርካሪ ድልድዮች፣
• 3 ዘመናዊ የእግረኛ ድልድዮች፣
• አጠቃላይ ከ240 ኪ.ሜ በላይ መንገድና ተያያዥ መሠረተልማቶች፣
2. የትራንስፖርት ስርዓት
• በአንድ ጊዜ 6,369 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 32 ዘመናዊ ፓርኪንጎች (ከዜሮ ወለል እስከ ሶስት ቤዝሜንት ያላቸው)፣
• በአንድ ጊዜ 517 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም የሚያስችሉ 9 የባስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣
• በአንድ ጊዜ 268 ባሶችንና ታክሲዎችን ለአጭር ጊዜ የመጫንና ማውረድ አገልግሎት የሚሰጡ 85 የመንገድ ዳር የባስና ታክሲ ቤይ፣
• 50 ኪሎ ሜትር የትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል የብልህ (ITS) ስርዓት።
3. የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስራዎች ፦
• 430 ዘመናዊ ስማርት ፖሎች (ስክሪንና ዘመናዊ የደህንነትካሜራዎች ያሉት)
• ከተማችን የደህንነት ካሜራዎች ባለቤት እንድትሆን 48 ኪሎ ሜትር የስርዓት ዝርጋታ
• 1,582 መደበኛ የመንገድ መብራቶች (Normal street lights)
• ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ የአደጋ መንስዔ የሆኑ ያረጁና እንደሸረሪት ድር የተተበተቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች እና ፖሎችን አንስቶ ወደ ምድር ውስጥ የመቅበር ስራ (ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ ተከናውኗል)
4. የህዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎች መስፋፋት
• 32 የውሃ ፏፏቴዎች፣
• 20 ሄክታር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ መልሶ ማልማት ስራዎች
. 8 ወንዞች በተቀናጀ መልኩ እየለሙ ይገኛሉ፡፡
• 120 ዘመናዊ የመንገድ ዳር የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets) ፣
• 50 ሄክታር በላይ የከተማ አረንጓዴ ልማት ስራዎች፣
• 70 የህዝብ መናፈሻ ስፍሪዎች እና የፈጣን ምግብ አገልግሎት መሸጫ ቦታዎች
5. የውሃና ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች
• 48 ኪ/ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ስርዓት ዝርጋታ
• ከ17.8 ኪ.ሜ በላይ አዲስ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ዝርጋታ፣
• ከ69 ኪ.ሜ በላይ (6 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ የውሃ ማሰራጫ መስመር እና 63 ኪሎ ሜትር መለስተኛ የውሃ ማሰራጫመስመር) ዝርጋታ፣
• ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚውል ባለ 110 ሚሊ ሜትር HDPE የቧንቧ ዝርጋታን ተከትሎ 71 የፋየርሃይድራንት (Fire Hydrant) ደረጃ መትከል
6. የቴሌኮሚኒኬሽን መሰረተ ልማት ስራዎችን በተመለከተ
• ከ70 ኪሎ ሜትር በላይ የቴሌኮም ግንባታ ዳክት፣
• 75 ኪሎ ሜትር የመዳብ ኬብል ዝርጋታ፣
• 152 ኪሎ ሜትር የፋይበር ኬቢል አዘዋውሮ የመዘርጋት ስራ፣
• 57 የኔትዎርክ ማከፋፈያ ሳጥኖች ተከላ፣
• 1,627 ምሰሶዎች ተከላ፣
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.