ትጉሃን ወጣቶች ወጣትነት ህይወት ምዕራፋችሁ መልካም ስራ የምታከናዉኑበት ነዉ! አቶ ሞገስ ባልቻ
የአዲስ አበባ የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ" በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "የክረምት በጎ ፈቃድ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ኘሮግራም በአበበ ቢቄላ ስታዲየም አካሂዷል ።
በእለቱ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ሞገስ ባልቻ ኢትዮጵያ ያላትን በርካታ ማህበራዊ እሴቶች ከለዉጡ ወዲህ አጉልቶ በመጠቀም የአቅመ ደካሞችን ቤት አፍርሶ በማደስ ፤በበአላቶች ማዕድ በማጋራትና በማካፈል አይዞአችሁ አለንላችሁ በማለት ተዳክሞ የነበረውን የማህበራዊ እሴቶቻችን ይበልጥ መሰረት እንዲይዝ በማድረግና በመላው ሀገራችን እንዲሰፋ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ በጎነትን ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መርህ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።
በመልዕክታቸዉም ወጣቶች የወጣትነት ጊዜያቸዉ ራሳቸዉን በአካል ብቃትና በአዕምሮ ግንባታ የምታዳብሩበት ነጋችሁን የምትሰሩበት እና ወገናችሁን በመደገፍ ልታሳልፉበት የሚገባ ስለሆነ በበጎ ተግባሮች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ።
በእለቱ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ሚኒስትር ዴኤታ ኸይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በሀገር አቀፍ ደረጃ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዳስጀመሩት በማስታወስ በዘንድሮ የበጎነት አገልግሎት በ3 የሚኒስቴር ተቋማት የጋራ ቅንጅት 34 ሚሊዮን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ና ህብረተሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ ለአብሮነት ብሎም ለሰላም ግንባታ ስራችን የበኩላቸውን እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችንና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው በክረምት በጎ ፈቃድ ንቅናቄ 2 ሚሊዮን ወጣቶችና የስፖርት ቤተሰቦች በ14 የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እንደሚሰማሩ ገልፀዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.