ክብርት አፈ ጉባኤ ማጠቃለያ መልዕክት አስተላለፉ !
በበጀት ዓመቱ በተፈራረሙት ስምምነት መሰረት አስፈፃሚ አካላቱ ግቦቻቸውን ማሳካት መቻላቸውን በመገምገም ጥንካሬና ክፍተት በመለየት የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል።
/አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር/
ምክር ቤቱ ላለፉት አምስት ተከታታይ ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን የተቋማት የበጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በስኬት አጠናቋል።
በመድረኩ በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ሁሉም ቢሮዎችና ተጠሪ ተቋማት ሪፖርታቸውን አቅርበው አስገምግመዋል።
የመድረኩን መጠቃለል አስመልክቶ ክብርት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለመረጠን ህዝብ በገባነው ቃል መሰረት የከተማችን ነዋሪ የልማት ፣ የሰላም ፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ እየተፈቱ መሆኑን ፤ የከተማችን አስፈፃሚ አካላት የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለና እየተጠናከረ መምጣቱን ተገንዝበናል አፈፃፀማቸውም በየዓመቱ በጣም እየጨመረ መሆኑን በተጨባጭ ተመልክተናል ብለዋል።
አፈ ጉባኤ ቡዜና አገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደርን በተመለከተም ፣ የህዝብ አገልግሎት ጥያቄ በሚበራከትባቸውና ለብልሹ አሰራር ተጋላጭ በሆኑ ተቋማት የከተማ አስተዳደሩ ቅድሚያ ሰጥቶ ሪፎርም በማድረጉ እጅግ ተስፋ ሰጪ ለውጥ ማምጣቱን በተጨባጭ አረጋግጠናል ብለዋል። በተለይም ሪፎርሙ የተቋማትን አደረጃጀት በማሻሻል ፣ ስራዎች ፍሰታቸው ተጠብቆ እንዲከወኑ ፣ አገልግሎት ፈላጊ ነዋሪ በብዛት በሚተምባቸው የታችኞቹ የአስተዳደር መዋቅሮች ለህዝብ ቅርብ በሆኑ ተቋማት እንዲሰጡ የሚያደርግ ፣ ብቃት ያለው የሰው ሀይል በየደረጃው እንዲመደብ የሚያደርግ ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ከተለምዶ የማኑዋል አሰራር ይልቅ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ የሚያደርግ፤ ለአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆ የሚሆኑ ህጎችና አሰራሮች እንዲሻሻሉ የሚያደርግ መሆኑ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እየታየ ነው ብለዋል።
ይህ ሪፎርም በጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ከተጠናከረ ደግሞ ነባር ችግሮችን እየቀረፈ ለውጡን ማስቀጠል የሚችል መሆኑን ምክርቤቱ ገምግሟልም ብለዋል።
በዚህ ረገድ ቀዳሚ ሚና ላላቸው ለፐብሊክ ሰርቪስ እና ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ግልጽ አቅጣጫም ተቀምጧል ብለዋል።
አፈ ጉባኤዋ አክለውም የከተማውን ነዋሪ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስፈልግ ሀብት ከከተማው መሰብሰብ ፣ ግለሰቦችንና ባለሀብቶችን በማሳተፍ ለልማትና ለበጎ ፈቃድ ስራዎች የሚያስፈልግ ፋይናንስ ማመንጨት መቻሉ የገቢ ዕድገት መጨመሩ እንዲሁም የተሰበሰበውን ሀብት መልሶ በልማት ላይ በማዋል ፣ ብልሽትና ብክነትን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ውጤት መታየቱን ተገምግሟል ብለዋል።
ከማህበራዊ ልማት አንፃርም ከመሰረተ ልማቶች ግንባታና መስፋፋት በተጨማሪ አገልግሎት አሰጣጣቸው ተሻሽሏል።
የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በተሰሩ ስራዎች የከተማ የከተማ ግብርናና የሌማት ቱሩፋት ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የተመለከትን ሲሆን ከዚህ የተወሰዱ ተሞክሮዎችን በማስፋት ከልመናና ተረጂነት ለመውጣት አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸው ታይቷል ብለዋል።
በመጨረሻም መድረኩ የምክርቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና አባላቱ ሁሉም በሁሉም ተቋማት ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው አድርጓል። ለቀጣይ ስራችንም ግብዓት የተወሰደበት ነው ብለዋል።
አስፈፃሚፈውም በተመሳሳይ ህዝቡ ምን ይላል የሚለውን መረጃ በእንደራሴው በኩል ያገኘበት እጅግ ጠቃሚ መድረክ ነበረ ሲሉ ክብርት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የማጠቃለያ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.