ዛሬ በአሰላ እና ደብረብርሃን የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርዓተ ትምህርት በዲፕሎማ መርሃግብር ስልጠና ተከታትለው ያጠናቀቁ 2027 የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራንን በዓድዋ ድል መታሰቢያ አስመርቀናል።
የመርሀግብሩ ዋና ዓላማ አዲስ አበባን ህጻናትን ለማሳደግ ምርጥ አፍሪካዊት ከተማ ለማድረግ የጀመርነውን ራዕይ ማሳካት ሲሆን ዛሬ ያስመረቅናቸውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ዙሮች 3685 መምህራንን አስመርቀን ወደ ስራ አስገብተናል።
ህጻንነት የሰው ልጅ በዕውቀት፣ በስነ ምግባር፣ በአካልና በአእምሮ እንዲሁም በሁለንተናዊ እድገት የሚገነባበት እድሜ ነው። በዚህ ጨቅላ እድሜ ተገቢውን ኢንቨስትመንት ካደረግን እና መልካም ዘርን ከዘራን ነገ ጣፋጭ እና መልካም ፍሬን በማፍራት የሚከፍለን ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በዚህ እድሜ ላይ ልዩ ትኩረት ያደረገውም ለዚሁ ነው። በመሆኑም ያልዘራነውን እንደማናጭድ ገብቶን ሁላችንም ይህንን ፕሮግራም በመደገፍ እንድናሳካው ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.