አዲስ አበባ ላይ እየሰራን ያለውን የስፖርት መሠረተ ልማት መስፋፋትን በተለይም የእግር ኳስ ሜዳዎችንን በማየት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሰጠኝ እውቅና እንዲሁም የዋልያዎቹ እና የሉሲዎቹ የበላይ ጠባቂ አድርጎ ሃላፊነት ስለሰጠኝ ከልብ አመሰግናለሁ::ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የእግር ኳስ ስፖርት ሕዝባችን በስስት የሚያየው እና ታሪካችንም ከጀማሪዎቹ ፣ ነገር ግን በውጤት ከኃላ የቀረን እና የስፖርት ቤተሰቡን እያስቆጨ የሚገኝ ቢሆንም ይህን ታሪክ ለመቀየር በጋራ በመስራት እግር ኳሳችንን ወደ ክብሩ ለመመለስ ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር በቅርበት መስራታችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.