በከተማችን በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማችን በበርካቶች የቀን ከሌሊት ልፋት ውብ ተደርገው በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ላይ ቆሻሻ የሚጥሉ እና ከተፈቀደላቸው መንገድ ውጪ የሚሄዱ እንዲሁም ከተማችንን አረንጓዴ ለማድረግ በመንገድ አካፋዮች ላይ የተተከሉ ዛፎችን በግዴለሽነት በተሽከርካሪ በመግጨት ጉዳት ያደረሱ አካላት ተቀጡ::

በዚህም 3 ተቋማት ከተፈቀደ ቦታ ውጪ ቆሻሻ በመጣል እንደየጥፋት ደረጃቸው 100 ሺሕ ፣ 50 ሺ እና 20 ሺሕ ብር የተቀጡ ሲሆን 5 አሽከርካሪዎች በመንገድ አካፋይ ላይ የተተከሉ ዘንባባ ዛፎችን ገጭተው በመጣላቸው እንደየጥፋት ደረጃቸው ከ150 እስከ 300 ሺሕ ብር እንዲሁም 11 ሰዎች ከተፈቀደው የእግረኞች መንገድ ውጪ በመሄዳቸው ከ150 እስከ 1000 ብር ተቀጥተዋል:: 

ነዋሪዎቻችን እነዚህ ደረጃቸውን ጠብቀው የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በተፈቀደው መንገድ ብቻ በመጠቀም እና በመንከባከብ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ከቅጣት እና ከትራፊክ አደጋ እንዲከላከሉ ለማሳሰብ እንወዳለን::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.