የ #አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ #አረንጓዴዓሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት ሥራችን ያስቀመጥነውን ግብ በሚያሳካ መልካም አጀማመር ላይ ይገኛል። የኅብረተሰባችንም የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነው። ዛሬ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ የአፕል ችግኞችን ተክለናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

በአካባቢው የተደረገውን የዘንድሮውን ችግኝ ተከላ ለየት የሚያደርገው ቀድሞ የነበረው የባህርዛፍ ሽፋን ተወግዶ በሀገር በቀል የእርከን ሥራ እና ተክል የተተካ መሆኑ ነው። 

ከሀረር አካባቢ እና ከኮንሶ የመጡ ህዝቦቻችን አፈር እንዳይሸረሸር የሚያደርገውን ጊዜ የማይሽረውን ክህሎታቸውን አካፍለውናል። በከተሞች የምንሠራውን የአረንጓዴ አሻራ ጥረቶቻችንን በጋራ በማስፋፋት የአዲስ አበባን አረንጓዴ ሽፋን መጨመር እንችላለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.