የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ውጤቱ ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አድርገዋል።

በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።

የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው በቀጣይ ጥቂት ቀናት የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በተመሳሳይ ይፋ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85,219 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 67,903 የሚሆኑት ማለትም 78.9 በመቶ ያህሉ 50 በመቶ እና በላይ ማምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ አስታውቀዋል።

ተማሪዎችም ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት እንደሚችሉ ቢሮው በመረጃው አመልክቷል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.