የአዳስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአረንጓዴ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዳስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በለሚኩራ ክ/ከተማ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን "የምትተክል ሀገር ፤ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በቦሌ አራብሳ ወረዳ 04 አስተዳደር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ። 

በመረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳሉት ሁሉም ሰው በራሱ ተነሳሽነት ችግኝ መትከሉን አጠናክሮ መቀጠል እና የተተከሉ ችግኞችን ክረምት ነው ብለን ሳንዘናጋ በመንከባከብ ኃላፊነታችን መወጣት እያስፈልጋል ብለዋል።

እንደ ከተማ አስተዳደር በዚህ ክረምት ለመትከል የታቀደውን ለማሳካት ሰፊ ንቅናቄ ተፈጥሮ እየተተከለ መሆኑን ተናግረው የችግኝ አተካከል ስርዓትን ተከትለን በመትከል ከፍተኛ የፅድቀት እንዲኖር የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። 

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታረቀኝ ገመቹ እንዳሉት በተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሀ ግብሮችን አከናውነናል በመሆኑ ማህበረሰቡ ችግኝ የመትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ የማፅደቅ ስራ ላይ ልዩ ትኩረት ልሰጠው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። 

ቢሮው ከዚህ በፊት መዋቅሩን በማስተባበር በተለያዩ ጊዜ የኢንዱስትሪ ማዕከላት እና ሌሎችች ቦታዎች ችግኝ ስተክል መቆየቱ ተገልፆዋል።

ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.