ኤኤምኤን በይዘቶቹ የሕዝብ ድምፅ ከመሆን ባሻገር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኤኤምኤን በይዘቶቹ የሕዝብ ድምፅ ከመሆን ባሻገር በሀገራዊ ተልዕኮዎች እና በበጎ ተግባራት ላይም አሻራውን እያኖረ የሚገኝ ቀዳሚ የመገናኛ ብዙኃን ነው - አቶ ካሳሁን ጎንፋ

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤኤምኤን) በይዘት እና በአቀራረቡ የሕዝብ ድምፅ ከመሆን ባሻገር በተለያዩ ሀገራዊ ተልዕኮዎች እና በጎ ተግባራት ላይም አሻራውን እያኖረ የሚገኝ ቀዳሚ የመገናኛ ብዙኃን ነው ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ። 

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የዘንድሮው 6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ላይ ተካፍለዋል። 

አዲስ አበባ መርሐ-ግብሩን ካስጀመረች ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክም ይህን መርሐ-ግብር በእንጦጦ ፓርክ አከናውኗል። 

አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በተለያዩ መንገዶች መረጃዎችን ለኅብረተሰቡ በማድረስ የሕዝብ ድምፅነት ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም አሻራውን በማኖርም ቀዳሚ ተቋም ነው። 

የኤ ኤም ኤን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተቋሙ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ እየተወጣ መሆኑን ጠቅሰው፣ በበጎ ተግባራት ላይ የተገበራቸውን ተግባራት አንሥተዋል።

ተቋሙ በይዘት እና በአቀራረቡ የሕዝብ ድምፅነት ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር በችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩም ለቀጠዩ ትውልድ የሚተርፍ ተግባርንም እየከወነ ነው ሲሉ ገልጸዋል።  

በመርሐ-ግብሩ ላይ ተካፍሎ አሻራን ማሳረፍ ብቻ ሳይሆን የተተከሉ ችግኞችን ተንከባክቦ ማሳደጉ ላይም ትኩረት ይሰጠው ብለዋል። 

በመርሐ-ግብሩ የተሳተፈፉ የተቋሙ ሠራተኞችም በዚህ ሀገራዊ አሻራ ላይ ታሪካዊ ተሳታፊ በመሆናችችን እድለኞች ነን ሲሉ ገልጸዋል። 

 

#Addisababa 

#Ethiopia

ለተጨማሪ መረጃ👇👇👇

https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.