የአዲስ አበባ ለውጥ ሃብትን በመቆጠብ፣ ለተገቢው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ለውጥ ሃብትን በመቆጠብ፣ ለተገቢው የጋራ ልማት ብቻ በማዋል እና ለዜጎች ትኩረት በመስጠት እየተተገበረ ያለ፣ ፈጠራና ፍጥነት ላይ የተመሰረተ፣ ቀጣይነት ያለው ነው።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ስራው የከተማችን ነዋሪዎች ትብብር ጎልቶ የታየበት እና ከከተማ እስከ ፌደራል ያሉ የመሰረተ ልማት መስሪያ ቤቶች ቅንጅት የተረጋገጠበት ነው።

በመሆኑም፣ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንጻዎቻችሁን በከተማችን ስታንዳርድ እና ዲዛይን መሰረት ያሳመራችሁ እንዲሁም ለእግረኛ መተላለፊያ እንዲሆን ምቹ በማድረግ የሰራችሁ የህንጻ ባለቤቶች፣ ከሁሉም በላይ የመገልገያ ቦታዎችን ክፍት በማድረግ ከተማችን 24 ሰዓት የማትተኛ እና የምትንቀሳቀስ እንድትሆን አገልግሎት አሰጣጣችሁን የለወጣችሁ፣ በአጠቃላይ የኮሪደር ልማቱን ዓላማ ያሳካችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ሁሉ በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። 

ስንተባበር እንዲህ አይነት ፈጣን፣ ሰፊ ፣ ጥራትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ማስመዝገብ እንችላለን። አሁንም ይህን ስራ በሌሎች የከተማችን አካባቢዎችም ስለምናስፋፋው በላቀ ትብብር እና በቅርበት እጅ ለእጅ ተያያዘን መስራታችንን እንድንቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.