በቦሌ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ
በቦሌ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ስር ውሏል።
የክፍለ ከተማው የንግድ ፅ/ ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሸምሲያ ሀሰን እንደገለፁት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራን ተከትሎ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርት ደብቀው ባከማቹ የንግድ ድርጅቶች ላይ ርምጃ ተወስዷል።
በክፍለ ከተማው ወረዳ 7 በተደረገ ክትትል 25 ኩንታል ጤፍ እና 9144 ካርቶን ዘይት በሕገወጥ መንገድ ተከማችቶ በቁጥጥር ሥር መዋሉንም አስታውቀዋል።
እስካሁን 31 የሚደርሱ የንግድ ድርጅቶች በሕገወጥ ተግባር ተሰማርተው የተገኙ በመሆናቸው መታሸጋቸውንም መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
AMN
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.