አዲስ አበባ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወን ችላለች፡- አቶ ጃንጥራር አባይ
አዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወን መቻሏን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ ያዘጋጀው 11ኛው ዙር የፌዴራል፣ የክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዙሪያ የተዘጋጀ ጉባኤ ተካሂዷል።
በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከተማ አስተዳደሩ ከትምህርት ቤት ምገባ ጀምሮ የተለያዩ ሰው ተኮር መሠረተ ልማቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ በመተግበር ለአገልግሎት አብቅቷል ብለዋል።
በቀጣይም በከተማዋ እየጨመረ የመጣውን የነዋሪዎች ቁጥር ተከትሎ በሚደረጉ የማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ ሲቪል ማህበራት እና ድርጅቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.