ኮሙኒኬሽን ቢሮ “ የምትተክል ሀገር የሚያፀና ት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ኮሙኒኬሽን ቢሮ “ የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ መረሀ-ግብር አካሄደ።

የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ‹‹ምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል ዛሬ ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም በእንጦጦ ፖርክ ውስጥ 2ተኛ ምዕራፍ 2ተኛ ዓመት የአረጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ፣ክብርት ዘይነባ ሽኩር የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶቸና ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ የአዲስ አበባ አረንጓዴ ውበት እና ፅዳት ቢሮ ሃላፊ :የቢሮው ምክትል ኃላፊዎች ፣የኮሙኒኬሽን መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች ፣አርቲስቶች ፣የሚዲያ ተቋማት :ባለሃብቶች ፣ ጋዜጠኞች እና ታዋቂ ሰዎች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል ።

በመርሀ -ግብሩ መክፈቻ ላይ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ እናታለም መለስ እንደተናገሩት ፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስናኖር ሃገር በቀል ችግኞችን በብዛትና በጥራት በእንጦጦ ፓርክ አኑረናል ፤የዛሬው መርሃ ግብር አረንጓዴ አሻራችንን ብቻ ለማሳረፍ ሳይሆን ትላልቅ ሃሳቦችንና ታሪክን ጭምር በትዉልድና በሃገር ላይ ለመትከል ነዉ፡፡

ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የአካባቢ ጥበቃ መርህን በመከተል ለአየር ንበረት መስተካከል አውንታዊ አስተዋጽኦ የሚኖራቸውን ሀገር በቀል ችግኞች በህብረት ከመትከል ባለፈ መጽደቃቸውንም የምንከታተልም ይሆናል ብለዋል ።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች በበኩላቸው• አገር በትውልድ ቅብብሎሽ ይቀጥላል ፣ ነገን በማሳብ ጎዳናዎቿ ንጹህና አረንጓዴ ፣ተራራዎቿ ለምለም የሆነች አገር ለመፍጠር እንደ መንግስት እየተከናወነ ያለውን ውጤታማ ሥራ ከግብ ለማድረስ የኮሙኒኬሽን መዋቅሩ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በመረሀ ግብሩ ላይ 2 ሺህ አምስት መቶ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት አገር በቀል ችግኞች ተተክለዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.