ዛሬ ጠዋት የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ጠዋት የ2016 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ስራ አፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማከናወን ጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል እና ከተማችንን ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በ2016 በጀት ዓመት ከያዝነው አጠቃላይ እቅድ በአማካይ ከ91% በላይ የሚሆነውን ማሳካት የቻልን ሲሆን ፤ ይህም አዲስ የስራ ባህል በመተግበር ያሳካነው ነው።

በግምገማችንም በ2016 በጀት ዓመት ስኬቶቻችንን በማላቅና በማስፋፋት፣ የጥንካሬዎቻችንን ምንጭ በመለየት እንዲሁም ጉድለቶቻችንን በመሙላት እና በማረም ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት ለኑሮ የተመቸች ውብ አበባ የሆነች ከተማ ለመገንባት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

 

 ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.