በ2016 በሠላምና ፀጥታ ስራ አፈፃፀም በተመለከተ፤-
👉በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በየአካባቢው ፤በብሎክ የማህበረሰብ አቀፍ ምክክር መድረኮች እና የአካባቢን ፀጥታ በመጠበቅ ፣ለወንጀለኞች መደበቂያ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችንና የስጋት ምንጮችን ለይቶ መከላከል እንዲቻል በድግግሞሽ እስከ 6.3 ሚሊዮን የሚደርሱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎ ማረጋገጥ ተችሏል።
👉የወንጀል ድርጊቶችን በመቀነስ ረገድ፡ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ ህገ ወጥ የገንዘብና የጦር መሳሪያ ዝውውር እና ሃሰተኛ ሰነድ መጠቀም፡ ከከባድና ቀላል ወንጀል፣ የትምህርት ቤቶችን ደህንነት ከሚያውኩ ድርጊቶች፣ ከቤቲንግ ቤቶች፣ ከግጭቶች፣ ከኢኮኖሚ አሻጥርና ህገ ወጥ የንግድ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ሕግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት 22,251 የወንጀል ድርጊቶችን በመለየት፣ የመከላከል እና እርምጃ የመውሰድ ሥራ በመሰራቱ በአጠቃላይ የወንጀል ምጣኔ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር እየቀነሰ መጥቷል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.