#በበጀት ዓመቱ 18,091 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለህዝብ ክፍት ተደርገዋል ::
በ2016 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈፃፀም ተብለው ከተነሱት መካከል በአዲስ አበባ የተከናወኑ አጠቃላይ ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ልማቱ እንዲናበቡ ተደርገው በመሰራታቸው የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ መሰረት መሆናቸው ይገኝበታል::
በ2016 የበጀት ዓመት ከተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ የሀገራችንንና የከተማችንን ገፅታ ከፍ ያደረጉ ታላላቅ ኘሮጀክቶች፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የነገዋ ሴቶች ተሐድሶ እና የልህቀት ማበልጸጊያ ማዕከል፣ የቃሊቲ - ቱሉዲምቱ- ቂሊንጦ መንገድ ተሻጋሪ ድልድዮች፣ የዳቦና እንጀራ ፋብሪካዎች ፣ ሶስት ግዙፍ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም የጉለሌ የተቀናጀ ልማትን ለአብነት ማንሳት ይቻላል።
ከዚህም በተጨማሪ አዲስ የስራ ባህል የተተገበረበት እና በአጭር ጊዜ የከተማችንን ገጽታ መቀየር የቻለ የኮሪደር ልማት ስራ በማጠናቀቅ ለነዋሪው በተገባው ቃል መሰረት ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ የመገንባት ስራችን ተጠናክሮ ቀጥሏል::
የአቃቂ ግብርና ምርት እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የገበያ ማዕከልም ተጠናቆ ሥራ ጀምሯል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.