የንግድ ስርዓቱ ፍትሐዊና ቀልጣፋ ማድረግን በተመ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የንግድ ስርዓቱ ፍትሐዊና ቀልጣፋ ማድረግን በተመለከተ:-

👉በከተማችን ሚዛናዊና ፍትሃዊ የንግድ ሥርዓት በማስፈንና ፈጣን ቀልጣፋና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ በመሆኑ በህገወጥ ንግድ ሥራ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይም የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

👉በበጀት ዓመቱ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ለማሻሻል የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ነጋዴዎች ቁጥርን ከማሳደግ አንፃር 74,767 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 77,994 (ከ100% በላይ) ማከናወን የተቻለ ሲሆን 351,549 የንግድ ሥራ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 330,419 (94%) ማከናወን ተችሏል።

👉የኑሮ ውድነትን ለማቃለልና የምርት አቅርቦት ክፍተቱን ማጥበብ የሚያስችሉ በከተማዋ የመግቢያ በሮች (በአቃቂ፣ ኮልፌ፣ ለሚኩራ እና ንፋ-ስልክ ላፍቶ ክ/ከተሞች) ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ አዳዲስ የገበያ ማዕከላትን ሥራ በማስጀመር አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ ምርት እንዲያቀርቡ እና ሸማቹም በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ በማዕከላቱ የገበያ ሰንሰለቱን በማሳጠር የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ላይ በገበያ ካለው ዋጋ ከ15-20% መቀነስ ተችሏል። 

👉አምራችና ሸማቹ በቀጥታ ግብይት የሚፈፅሙባቸው ሌላው የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን ወደ 193 በማስፋት ገበያውን በማረጋጋት ረገድ አስተዋፅኦ እንዲኖራቸው የማድረግ እንዲሁም የምርት አቅርቦትና ፍላጎት ችግሩን የሚፈታ በቂ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ሊያቀርብ የሚችል የንግድ ድርጅት ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ ሲሆን በከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን በማስፋት፣ በሌማት ትሩፋት ከታዩ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መካከል የወተት፣ የዶሮ ሥጋ፣ እንቁላል እና የማር ምርታማነት በማሳደግ እንዲሁም የጓሮ አትክልት በማምረት ባለን ጸጋ የከተማችንን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

👉መንግስት በድጎማ የሚያቀርባቸውን የመሠረታዊ ፍጆታ ሸቀጦች ለኅብረተሰቡ በፍትሃዊነት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር 468 ሺህ ኩንታል ስኳር ለማቅረብ ታቅዶ 365,568 (78%) ኩንታል ስኳር እንዲሁም 5.27 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለማሰራጨት ታቅዶ 5 ሚሊዮን ሊትር (95%) ማሰራጨት ተችሏል። እንዲሁም የዳቦ አቅርቦትን በቀን 6 ሚሊዮን ዳቦ ማምረት የሚያስችል አቅም መፍጠር ተችሏል።

👉በኅብረት ሥራ ማኅበራት ይስተዋል የነበረውን የሌብነትና ብልሹ አሰራር፣ በሚፈታ አግባብ የኢንስፔክሽን እና የኦዲት ሥራዎች እንዲሰሩ ተደርጓል። በኦዲት የተገኙ ጉድለቶችን በፍርድ ቤት፣ በሽምግልና ዳኝነት እና በምክክር ከ78.1 ሚሊዮን ብር በላይ ተመላሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በሌላ በኩልም የረጅም ጊዜ አርሶ አደሮች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበረውን በራስ ይዞታ ላይ የማልማት መብት ለማረጋገጥ ግልፅ አሰራር ተዘርግቶ ይዞታቸው በአግባቡ እንዲለካና የመጠቀሚያ ካርታ በመስጠት በዘመናዊ ከተማ ግብርና እና አቅም ያላቸው የተለዩዩ ኢንቨስትመቶች እንዲሳተፉ መደረጉ በዘርፉ ከታዩ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተጠቃሽ ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.