በበጀት ዓመቱ 859.47 ሄ/ር መሬት በውሳኔና በጨረታ ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
👉በ2016 የመሬት አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እንዲሁም ከሌብነት እና ብልሹ አሰራር ለመከላከል የተቀናጀ የመሬት አስተዳደር መረጃ ሥርዓት (integrated land management system) ተግባራዊ በማድረግ 723,101 ማኅደሮች ስካን ተደርገው ዘመናዊ የመረጃ ቋት ውስጥ በማስገባት 40 የመሬት አገልግሎቶች ኦንላይን እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል።
👉128,401 ቁራሽ መሬትና ኮንዶሚኒየም ቤቶች በፓርሴል ለማረጋገጥ ታቅዶ 179,512 (ከ100% በላይ) ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ለ73,109 ይዞታዎች የምዝገባ አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም አገልግሎት የተሰጠባቸው ማህደራት ላይ የሕግና የቴክኒክ አሰራር ኦዲት ተደርጎ በግኝቶቹ ላይ ማስተካኪያ እርምጃ ተወስዷል።
👉 የተለያዩ ፕሮጀክት ማለትም የኮሪደር ልማት፣ የመንገድ ፕሮጀክት፣ የልማት ተነሺዎች 6.2 ቢሊየን ብር ካሳ መክፍል የተቻለ ሲሆን በፕሮጀክቱ ለሚነሱ የልማት ተነሺዎች እጅግ በተቀላጠፈ ሁኔታ ለ2,538 ቦታዎች (33.4 ሄ/ር) መሬት ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
👉 የመብት ፈጠራ ሥራን በሚመለከት በበጀት ዓመቱ ለ17,583 መብት ለመፍጠር ታቅዶ 14,483 ለሚሆኑት መብት የመፍጠር ሥራ ተከኗውኗል፡፡
👉በበጀት ዓመቱ የመዋቅራዊ ፕላን አካል የሆነውና የከተማችንን ገጽታ የሚቀይር፣ በተለያዩ ጊዜያት የለሙ ሥራዎችን ሊያያይዝ የሚችልና፣ አጠቃላይ የከተማዋን እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ 1,435.6 ሄ.ር. የሚሸፍኑ የኮሪደር ልማት ፕላን እንዲሁም 1,365 ሄ.ር. የሚሸፍኑ 13 የአካባቢ ልማት ፕላኖች ፀድቀው ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.