በበጀት ዓመቱ ለ291,577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በበጀት ዓመቱ ለ291,577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል

👉በ2016 ለ300 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ291,577 ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ዘርፎቹ፡- የከተማ ግብርና ፣ ማኑፋክቸሪንግ ፣ ኮንስትራክሽን ፣ ንግድ እና አገልግሎት ዘርፎች ሲሆን። የሴቶች ተጠቃሚነት 51% ማድረስ ተችሏል፡፡

👉ለ10,800 ኢንተርፕራይዞች 2.1 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ ታቅዶ 7,539 ኢንተርፕራይዞችን የ2.5 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። ከመደበኛ ብድር 2.7 ቢሊዮን ብር ለማስመለስ ታቅዶ 2.6 ቢሊዮን ብር ማስመለስ የተቻለ ሲሆን ከተዘዋዋሪ ብድር ደግሞ 104 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 64.1 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ተደርጓል።

👉ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ለሚገኙ 551 አምራች ኢንዱስትሪዎች የመሳሪያ ሊዝ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 466 ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

👉ስትራቴጂክ ገቢ ምርት የሚያመርቱ 1,295 አምራች ኢንዱስትሪዎች 4.3 ሚሊዮን ቶን ምርት በማምረት 1.86 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ለማዳን ታቅዶ 1,683 አምራች ኢንዱስትሪዎች 5.17 ሚሊዮን ቶን ምርት በማምረት 1.84 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ማዳን ተችሏል።

👉ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውል የመስሪያ ቦታዎችን ከማልማት አንፃር፡ 58 ማከናወን የተቻለ ሲሆን የመስሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማሳደግ 217 መገንባት ተችሏል፡፡

👉ለኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት የሚውል መሰረተ ልማት የተሟላላቸው 351 መስሪያ ቦታዎች ለማልማት ታቅዶ 350 የተከናወነ ሲሆን፣ 66.9ሺህ ካሬ ሜትር መስሪያ ቦታዎች ለኢንተርፕራይዞች ለማስተላለፍ ታቅዶ 54.2 ካ.ሜ ማስተላለፍ ተችሏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.