ዛሬ ማለዳ ልደታ ቤተክርስታያን አካባቢ ለልማት ተነሺዎች የሚተላለፍ ሁለት ባለ 9 ወለል የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን አስጀምረናል።
ቀድም ብለን ከጀመርናቸዉ ጋር ከ300 በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ነው። እነዚህ በፍጥነት በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶች ከልደታ ቆርቆሮ ሰፈርና ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ለልማት ለሚነሱ ነዋሪዎቻችን የሚሰጡ ዘመናዊና ለመኖር ምቹ ከመሆናቸው ባሻገር ለነዋሪዎች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ የንግድ ቦታዎችንም ያካተቱ ናቸው።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያለማቋረጥ ሁሌ ለሚያደርግልን አስተዋፆኦ በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግን እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.