#ቃል_በተግባር

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

#ቃል_በተግባር

ባለፉት አራት ወራት በተለየ ትኩረት የተከናወነዉ የኮሪደር ልማት ስራዎችና መልሶ ማልማት ተጠቃሾች ናቸው። 

  በዚህም መሰረት የፕሮጀክት ስራን በተመለከተ፦

1.የመንገድ መሠረተ ልማት

  👉ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ መንገድ፣

  👉ከ96 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 

  👉100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣

  👉4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ (underpass) መንገዶች፣

  👉5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣

  👉⁠2 የተሽከርካሪ ድልድዮች፣

  👉⁠3 ዘመናዊ የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች አካቷል፣

2. የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ፦

  👉በአንድ ጊዜ 6,369 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 32 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣  

  👉በአንድ ጊዜ 517 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸው 9 የባስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣  

  👉በአንድ ጊዜ 268 ባሶችንና ታክሲዎችን ለአጭር ጊዜ የመጫንና ማውረድ አገልግሎት የሚሰጡ ‘‘85’’ የመንገድ ዳር የባስና ታክሲ ማዉረጃ ቦታ፣

  👉50 ኪሎ ሜትር የትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል (ITS) መስመር ዝርጋታ፣

3. የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ፦

  👉እስክሪንና ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች የተገጠሙለት 450 ዘመናዊ ስማርት ፖሎች፣ 

  👉48 ኪሎ ሜትር የደህንነት ካሜራ መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣

  👉1,582 መደበኛ የመንገድ መብራቶች (Normal street lights)፣

  👉ከ96 ኪሎ ሜትር ለአደጋ መንስዔ የኤሌክትሪክ መስመሮች እና ፖሎችን አንስቶ በምድር ውስጥ መቅበር ሥራ፣ 

4. የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት፦

  👉32 የውሃ ፏፏቴዎች፣

  👉20 ሄክታር የሚሸፍን መልሶ ማልማት፣ 

  👉8 ወንዞች በተቀናጀ መልኩ ማልማት፣

  👉120 ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣

  👉50 ሄክታር በላይ የከተማ አረንጓዴ ልማት ሥራዎች፣

  👉70 የሕዝብ መናፈሻ ሥፍራዎች እና የፈጣን ምግብ አገልግሎት መሸጫ ቦታዎች፣

5. የውሃና ፍሳሽ ማስወገጃ ስርአቶች፦

  👉48 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታ፣

  👉ከ17.8 ኪ.ሜ በላይ አዲስ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ዝርጋታ፣

  👉ከ 69 ኪ.ሜ በላይ የውሃ ማሰራጫ መስመር ዝርጋታ፣

  👉ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚውል ባለ 110 ሚሊ ሜትር HDPE የቧንቧ ዝርጋታን ተከትሎ 71 የፋየርሃይድራንት (Fire Hydrant) መትከል፣ 

6. የቴሌኮሚኒኬሽን መሠረተ ልማት ሥራዎች፦

  👉ከ70 ኪሎ ሜትር በላይ የቴሌኮም መገልገያ ዳክት ግንባታ፣

  👉75 ኪሎ ሜትር የመዳብ ኬብል ዝርጋታ፣

  👉152 ኪሎ ሜትር የፋይበር ኬብል አዘዋውሮ የመዘርጋት ሥራ፣

  👉57 የኔትዎርክ ማከፋፈያ ሳጥኖች ተከላ፣

  👉1,627 ምሰሶዎች ተከላ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

👉በስራው ሒደት 5ዐ,ዐዐዐ ሰዎች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን፣ የስራው ፍጥነትና ስፋት ከዚህ በፊት በአመታት እንኳን ሲሰራ ከነበረው የላቀ አስደናቂ ስራ በወራት ማከናወን 

ተችሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.