የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማችንን አጠናቅቀናል
የበጀት ዓመቱ የገቢ አሰባሰብ አቅማችንን 44 % አሳድገን ያሰበሰብንበት፣ በኮሪደር ልማት ስራዎቻችን አዲስ አበባን ከቆሻሻ በማጽዳት እንደ ስሟ ውብ አበባ ያደረግንበት፣ የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የሰው ተኮር ስራዎቻችንም የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉበት፣ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ አብሰው ማህበራዊ ፍትህን ያነገሱ ስራዎችን የሰራንበት እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደጎም 11 ቢሊዮን ብር ስራ ላይ ያዋልንበት ነበር።
በጀታችንን 63 % ለልማት በማዋል የህዝብን ሀብት ከምዝበራ ታድገናል። ለህዝብ ግልጋሎት ክፍት የተደረጉት ከ18 ሺሕ በላይ ፕሮጀክቶች ማንንም ወደኋላ ያልተው፣ አካታች ልማት ሲሆኑ በመንግስት እና ህዝብ ተሳትፎ በተሰራው የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄም 17.5 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የከተማችን የአረንጓዴ ሽፋን ማሳደግ ችለናል።
ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ በ10 ተቋማት ጠንካራ ሪፎርሞች እና አሰራሮችን የዘረጋንበት እንዲሁም አቅመ ደካሞችን እና የሀገር ባለውለታዎቻችንን የደገፍንበት ነበር።
ከህዝብ ጋር ባደረግናቸው በርካታ ውይይቶች የተለዩ ችግሮችን በተለይም ሌብነት፣ ጉቦኝነት፣ ብልሹ አሰራርን እንዲሁም በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያለውን ውስንነት በቁርጠኝነት በማስተካከል ለህዝባችን በገባነው ቃል መሰረት የምንሰራ ይሆናል።
ባመጣናቸው አመርቂ ውጤቶች እና ለውጦች ሳንወሰድ ውስንነቶች ላይ አፋጣኝ እርማት እየወሰድን ፣ ጥንካሬዎቻችንን በማስቀጠል አሁንም አዳዲስ አሰራሮችን በመተግበር ለነዋሪዎች ምቹ የሆነች ከተማ መገንባታችንን እንቀጥላለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.