
በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ከማዕከል እስከ ወረዳ ላሉ ተቋማት እውቅና እና ማበረታቻ ሰጥተናል::
ከሸለምናቸው መካከል
ከተቋማት:-
1. ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ - 1ኛ
2. ትምህርት ቢሮ - 2ኛ
3. ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ - 3ኛ
4. ኮሙኒኬሽን ቢሮ - 4ኛ
5. ሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት - 5ኛ
6. ፍትህ ቢሮ- 6ኛ
ከክፍለከተማ
1. ቦሌ ክፍለከተማ - 1ኛ
2. ቂርቆስ ክፍለከተማ - 2ኛ
3. አዲስከከተማ ክፍለከተማ - 3ኛ
ከሁሉም ክፍለከተሞች ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ ወረዳዎችም እውቅና ሰጥተን አበረታተን ለሚቀጥለውም ዓመት አደራ ብለን ሸኝተናል::
እውቅናው በቀጣይነት ህዝብን ዝቅ ብሎ ለማገልገል እና የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የሚያነሳሳ ፤ በተቋማት መካከል ጤናማ የሥራ አፈጻጸም እና ውድድር እንዲዳብር የሚያደርግ እንዲሁም ዝቅ ያለ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማትን በቁጭት የተሻለ እንዲሰሩ የሚያደርግ እና ተቋማትን የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያደርግ ነው::
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.