አዲስ አበባን የውበት አክሊል ያጎናጸፋት ተጨማ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ አበባን የውበት አክሊል ያጎናጸፋት ተጨማሪ ብስራት የመገናኛ - ሲኤምሲ የኮሪደር ልማት !!በበጀት ዓመቱ የመንግሥት እና የህዝብ አቅሞችን አስተባብረን መስራት በመቻላችን ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ችለናል ፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ

24 ሰዓታት የደራች የአፍሪካ ፈርጥ የሆነች እንደስሟ ውብ አበባ ከተማን ለመገንባት የሰነቅነው ራዕይን ዕውን ለማድረግ የምንሰራው የኮሪደር ልማት ስራችን አካል የሆነው የመገናኛ - ሲኤምሲ መንገድ አጠናቅቀን ዛሬ ምሽት መርቀን ለህዝብ ግልጋሎት ክፍት አድርገናል::

የጸዳችና የተዋበች አዲስ አበባን ዕውን ለማድረግ በተለወጠ አዲስ ዕይታና የስራ ባህል የሰራናቸው ስራዎች ከተማችንን የውበት አክሊል አጎናጽፈዋታል::

በዚህ ስራ ላይ የተሳተፋችሁ ፣ የመራችሁ ፣ ያስተባበራችሁ ፣ የህዝብን ሀብት ከብክነት የታደጋችሁ ፣ የጸጥታ አካላት ፣ ይዞታዎቻችሁን ለከተማችሁ ልማት የለቀቃችሁ ባለይዞታዎች እና ከሁሉም በላይ የከተማችን ነዋሪዎችን ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

በላቀ ሕብረትና ወንድማማችነት ወደተለምነው ብልጽግናችን በፍጥነት እንገሰግሳለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.