
የ5.7 ኪ/ሜ ርዝመት ያለው እና ሰፋፊ የህዝብ የጋራ መገልገያ ስፍራዎችን ለነዋሪው እነሆ ያልንበት ከመገናኛ - ሲኤምሲ አደባባይ ኮሪደርን ዛሬ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል::
ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰሩት የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲገለገልበት እና ሲዝናናበት እንዲሁም በየኔነት መንፈስ ሲንከባከበው በማየታችን ደስ ብሎናል::
ጀመርን እንጂ አልጨረስንም ፣ አዲስ አበባን ቃል በገባነው መሰረት በተሟላ መልኩ እንደ ስሟ ውብ አበባ እንድትሆን እጅ ለእጅ ተያይዘን ቀሪ የኮሪደር ስራችንን እያሰፋን እንሄዳለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.