እንኳን ደስ ያለን/ እንኳን ደስ ያላችሁ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በከተማዉ ከሚገኙ 56 አስፈፃሚ ተቋማት መካከል የ4ተኛ ደረጃን በማግኘት ዕውቅና ተበረከተለት፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የ2016 በጀት ዓመት የተቋማት የስራ አፈፃፀም ምዘና ይፋ መደረጉን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በበጀት ዓመቱ ባስመዘገበው የላቀ ውጤት በአስተዳደሩ ከሚገኙ 56 አስፈፃሚ ተቋማት ውስጥ የ4ተኛ ደረጃን በማግኘት ዕውቅና ተበርክቶለታል።
በከተማችን እያደገ የመጣውን አልሞ የመፈጸም ብቃትንና የተናበበ የመንግስትና የህዝብ ቅንጅታዊ የልማት ውጤታማነት አጀንዳ በመትከል፤ ሥልጡን ከተሜነት እና በጎ የሥራ ባህል እንዲጎለብት ፤ ሀሳብን በሀሳብ የመሞገት አቅም እንዲያድግ ቢሮዉ በትጋት ሲሰራ መቆየቱንና ለዚህ ዉጤት መብቃቱን ገልፃል፡፡
በ2017 በጀት ዓመትም ቢሮዉ ይበልጡን እንደሚተጋ እየገለፀ የአዲስ አበባ ከተማ ማህበረስብ ትክክለኛ እና ወቅታዊ የስራ መረጃ እንዲያገኝ እና ተግባቦት እንዲያድግ ከመረጃ ተቀባይነት የመረጃ ምንጭ በመሆን አስተዋጽዎ ላደረጉ በየደረጃው ለሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅራችን እና ባለድርሻ አካላት ምስጋናችንን እያቀረብን በድጋሜ እንኳን ደስ ያላችሁ! እንኳን ደስ ያለን! ለማለት እንወዳለን!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.