ኃላፊነት ባልተሰጠዉ ሰራ ዉሰጥ በመግባት ሀሰተኛ እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ህዝብን የሚያደናግሩና በተለያየ ጥፋት ዉሰጥ የሚሳተፉ የመንግሰት አካላትን ተከታትሎ እርምጃ እንደሚወሰድ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ገልጿል።
ከአፍሪካ ህብረት ጫፍ እስከ ቡልጋሪያ በሚከናወነው የኮሪደር ልማት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይፈርሳል በሚል የተሳሳተ መረጃ የሰጠ የቂርቆሰ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሰዩም መኮንን በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስታወቀ።
የኮሪደር ልማት የከተማዋን ነዋሪ ጥያቄ መሰረት አድርጎ እየተከናወነ ነው ያለው አስተዳደሩ ማንኛውም ውሳኔ በመንግስት ብቻ ሳይሆን ከህዝብና ከተቋማት ጋር በመነጋገር የሚፈፀም በመሆኑ የመንግስት አካል በመምሰልና ከመንግስት ፍላጎት ውጭ የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ህዝብን ከመንግስት ጋር የሚያጋጩ አካላትን በቀጣይም እንደማይታገስ አስተዳደሩ አክሎ ገልጿል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ እንዲህ ዓይነት የተሳሳተ መረጃ የሚሰጡ አካላትን ሲያገኝ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበሩ የጠየቀው አስተዳደሩ የቤተክርስቲያኑ አባቶችና ምዕመናን ለሰጡት ትዕግስት የተሞላበት መረጃ ምስጋናውን አቅርቧል።
ዘገባው የቂርቆስ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ነው
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.