ባለስልጣኑ በከተማው የልማት ኮሊሪደር ሆን ብለው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በከተማው የልማት ኮሊሪደር ሆን ብለው በቸልተኝነት የደንብ መተላለፍ በፈጸመ ግለሰብ ላይ እርምጃ ወሰደ::

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሠሌዳ ቁጥር ኮድ 2 C 28053 አ.አ የቤት መኪና አሽከርካሪ ግለሰብ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ መጠሪያው ቦሌ ማተሚያ አካባቢ የልማት ኮርደር ላይ በተሽከርካሪ ውስጥ በመሆን ባልተፈቀደ ቦታ ላይ የሲጋራ ቁራጭ ሆን ብሎ በቸልተኝነት በመጣል በህብረተሰቡ እንዲያነሳ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ባለመሆን አምልጦ ለግዜው ቢሠወርም በአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ብስለት በተሞላበት ብርቱ ክትትል ከነተሽከርካሪው በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ሥር ውሏዋል።

ግለሰቡ የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 150/2015 በተሻሻለው የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት 2000/ሁለት ሺህ ብር/ ተቀጥቷል ።

የተሰራው ልማት አዲስ አበባን ውብ ጽዱ በማድረግ የከተማዉ ህዝብ እንዲጠቀምበት ፣የቱርስት መስህብና ሌሎች በአለማችን የሚገኙ ከተሞች የደረሱበትን ዕድገት ደረጃ ለማድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌት ተቀን በመሥራት ለህዝብ ጥቅም በማዋል ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረጉ ይታወቃል።

ባለስልጣኑ አንዳንድ ግድ የሌሽ ግለሠቦች የተሠራውን ልማት ላይ ሆን ብለዉ በመኪና ሲገጩ ስያበላሹ፣ ያልተፈለገ ደረቅ ቆሻሻ ማለትም ሶፍት ፣የውሃ ፕላስቲክ ፣የሲጋራ ቁራጭ ፣የመሳሰሉትን በሚጥሉ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ይቀጥላል።

የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ዕለት በተወሰደዉ ቅጣት መረጃውን የሰጡንን የከተማዉን ነዋሪዎች ከልብ እያመሠገንን አሁንም ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች አጥፊዎችን መረጃ በመስጠት የጀመረውን ጥቆማ አጠናክሮ እንዲቀጥል በአክብሮት እንጠይቃለን።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.