የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክር ቤት አባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የምክር ቤት አባላት አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ !

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ"በሚል መሪ ቃል ለ6ተኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት እና አመራሮች እንዲሁም የከተማ እና የክፍለ ከተማ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በየካ ተራራ ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል::

ምክር ቤታችን ይህን አኩሪ እና አርአያነት ያለው ተግባር ፋና ወጊ መሆን ይጠበቅበታል ሰሉ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ ሙሀመድ ገልፀዋል:: 

ምክትል አፈ-ጉባኤዋ አክለው ችግኝ መተከሉ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለ ሆኖ የተተከሉ ችግኞችን ደግሞ የመንከባከብ ኃላፊነት አለብን ብለዋል።

ይህ ተግባር አረንጓዴና ውብ አካባቢን ለመፍጠር፣ የአየር ሁኔታ ተጽእኖዎችን ለመቋቋም እንዲሁም የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚያስችል በመሆኑ በተፈጥሮ የበለጸገችና ከአየር ብክለት የፀዳች አዲስ አበባን ለማስቀጠልና ለትውልዱ ለማውረስ ቃላችንን በተግባር ለውጠን ከነዋሪዎቻችን ጋር በመሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ባደረግነው ርብርብ የከተማችንን አረንጓዴ ሽፋን ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 17 በመቶ ከፍ ማድረግ ማስቻሉን ገልፀዋል:: 

ዘንድሮም በከተማ አስተዳደር ደረጃ 20 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመፃፍ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በየደረጃው ያለው የምክርቤት መዋቅር ብሎም መላው የከተማ ነዋሪዎ እንደከዚህ በፊቱ በዚህ ታላቅ ሃገራዊ ተግባር ላይ በመሳተፍ ለትውልድ የሚሻገር ፣ ሀገር የሚያፀና አረንጓዴ አሻራችሁን እንድታኖሩ ሲሉም ተናግረዋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.