“የአዲስ አበባ ውብ መንደሮች ኢትዮጵያ እንድትመስል የምንፈልገውን ብልፅግናዊ ምስል እየገለጡ ነው።” - የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ
የፓርቲያችን የከተማ ልማት እሳቤ በጠንካራ የስራ ባህል ተሟሽቶ፣ በህዝባችን ልማት ወዳድነት ከፍተኛ አቅም አግኝቶ፣በሀገር በቀል የግንባታ ጠበብቶቻችን ድምር ውጤት ፍሬ አፍርቶ አዲስ አበባ ላይ ውጤቱን ፍንትው ብሎ አይተነዋል ሲሉ ክቡር አቶ አደም ፋራህ ተናግረዋል::
በኮሪደር ልማት አቧራን አራግፈን የገለጥነው ውበት፣ከሰራን ሁሉም ሊለወጥ እንደሚችል ያረጋገጥነው እውነት፣ ዘወትር በትውልድ ልብ ውስጥ ተስፋ እና የይቻላል መንፈስን እንደሚጭር በፅኑ እናምናለን ያሉ ሲሆን የተገኘውን ውጤትም በአግባቡ በማጤን እና በቀጣይ በኮሪደር ልማት ስራ የተገኙ እምርታዎችን ቀምረን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንንቀሳቀሳለንም ብለዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.