በከተማዋ የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶች ልማት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት የልማት አጋርነታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የከተማዋን የመንገድ ሽፋንና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ሊያሳድግ የሚችል የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ላይ እና የአካባቢ ልማቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማስተላለፋ ይታወሳል።
በ3ኛ ዓመት 8ኛ መደበኛ ስብሰባው ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎም አዲስ አበባ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ የሚመጥን የመንገድ ልማት ኮሪደሮችን ለመገንባት የሚያስችል እቅድ ላይ የከተማዋን አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን እና ዘመናዊነት እንዲሁም የትራንስፖርት ፍሰት ወደ ላቀ ደረጃ ሊያሳድግ የሚችል የመንገድ ኮሪደር ልማቶች አንዱ በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚካሄደው የልማት ሥራ ሲሆን በዚህም መሰረት፥
* ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ.ሜትር) እና
*ከመገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ በአራት ኪሎ በኩል የአድዋ ድል መታሰቢያ አካባቢ ድረስ (6.4 ኪ.ሜትር) ያለው ፕሮጀክት ስራ በተደራጀ መልኩ ተጀምሯል።
በተመሳሳይ የመንገድ ኮሪደሩ ልማት የሚያካትታቸው፣
* ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ድልድይ (7 ኪ.ሜትር)
* ከፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ፣ በለገሃር ሜክሲኮ፣ በሳርቤት በኩል እስከ ወሎሰፈር (10 ኪ.ሜትር) ፤
* ከቦሌ አየር መንገድ እስከ መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ (4.9 ኪ.ሜትር) ፕሮጀክቶች ስራቸው የተጀመረ መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ።
የመንገድ ኮሪደር ልማቶች ሁለንተናዊ የመንገድ ዘመናዊነት ያሟሉ ከመሆናቸውም በላይ ዓለም አቀፍ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ገጽታ የሚያሻሽሉ መሆናቸው እሙን ነው።
በዚህም መሰረት በአራዳ ክፍለ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የግንባታ ሂደት አቶ ዣንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እየተከታተሉት ይገኛሉ።
የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቶቹ አዋሳኝ የወንዝ ተፋሰሶችን ያቀፉ፣ የሳይክልና ሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ፣ የከተማዋን ማስተር ፕላን ታሳቢ ያደረጉ በተጨማሪም አስፈላጊ በሆኑ የኮሪደሩ ቦታዎች ላይ ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ ተሸጋጋሪ ድልድዮች፣ ማሳለጫዎች እና ሰፋፊ መጋቢ መንገዶችን ያቀፈ ሲሆን የከተማ አረንጓዴ ልማትን ያካተተ እንደሚሆንም ታውቋል።
በዚህ የልማት ስራ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ የንግዱ ህብረተሰብ፣ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ መንግስት ተቋማት ትብብራቸውን የልማት አጋርነታቸውን በተግባር ያሳዩ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ በጋራ ለመስራት ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም መሰረትም የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተደራጀ መልኩ ወደስራ በመግባት መሰረተ ልማቱ የደረሰበትን በየእለቱ ቁጥጥርና ልዩ ክትትል በማድረግ ልማቱን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.