ዛሬ የከተማችንን አዲስ የከተማ ልማት ስትራቴጂ ዝግጅት በይፋ አስጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ይህም የከተማችንን እምቅ አቅሞችን በመለየት፣ እድሎችን በማንጠር፣ አዳጊ ፍላጎቶችን በማካተት እና ተግዳሮቶችን በመቀነስ የረጅም ጊዜ ርዕይ በመተለም ከተማችንን በዘላቂነት ወደፊት ለማስፈንጠር የሚያግዛትን የተቀናጀ፣ የተደራጀ እና አዳዲስ የከተማ ልማት እሳቤዎችን ያካተተ የልማት ፍኖት እንዲኖራት የሚያስችል ነው።
ይህንን በማሰናዳታችን በጅምር ላይ የሚገኙ እና ሳይንሳዊ ቅቡልነት ያገኙ፣ በተግባር የተፈተኑ የልማት ስራዎቻችንን ለማቀናጀት እና ለማስፋት እንዲሁም በሚቀጥሉት ዓመታት ከተማዋ የምትመራበትን የመዋቅራዊ ፕላናችንን ክለሳ ለመምራት የሚያስችሉንን አዳዲስ እሳቤዎች ለማካተት ያስችለናል።
በተጨማሪም የከተማችንን አዳጊ ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስፈልገንን ሀብት ለማሰባሰብ እንዲቻል እና ሁሉንም የልማት አቅሞች ለማቀናጀት የሚያስችል ግልጽ ራዕያችንን ለማጋራት ይጠቅመናል።
የከተማ ልማት ስትራቴጂ ዝግጅቱን በቴክኒክ የሚደገፈንን World Resources Institute / WRI እጅጉን አመሰግናለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.