የወንዝ ተፋሰስ መልሶ ማልማት ስራ ተጠናክሮ መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የወንዝ ተፋሰስ መልሶ ማልማት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ህዝቡ አደጋው ከመድረሱ በፊት መውጣት እንደሚኖርበት ተገለፀ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በትላትናው ምሽት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን እና በንብረት ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛዉ ገለፁ ፡፡

ኮሚሽነሩ እንደገለፁት መሰል አደጋዎችን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ሲያከናውን የነበረውን የወንዞችን መልሶ ማልማት ፕሮጀክት አጠናክሮ በማስቀጠል በነዋሪዎች ላይ የሚደርሰውን የአደጋ ስጋት መቀነስ እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ጋር በጋራ በመሆን ለነዋሪዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቶ ስፍራውን ለቀው በጊዜአዊነት በተዘጋጀላቸው ማረፊያ እንዲሄዱ በመደረጉ የጉዳት መጠኑ ሊቀንስ መቻሉንም ተናግረዋል ፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም ህዝቡ ከወንዝ ዳርቻ አደጋው ችግሩ ከመከሰቱ በፊት መውጣት እንዳለበት እና ወደፊትም በፈር ዞን ቤቶች ሲገነቡ የወንዝ ዳርቻ በፈር ዞን ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል::

በመጨረሻም በወንዝ ዳርቻ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.