ዛሬ በ14 የከተማችን ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በ14 የከተማችን ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች በ22 የስልጠና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 5180 ሰልጣኞችን አስመርቀናል::ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው 30 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ ፣ 70 በመቶውን ደግሞ የተግባር ስልጠና ከተከታተሉ በኋላ በኮሌጅ ደረጃ የብቃት ምዘና ተመዝነው ያለፉ ናቸው፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች በስልጠና ቆይታችሁ የጨበጣችሁትን ሙያ በራሳችሁ ጥረት በማዳበር ከሀገራችሁ አልፋችሁ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ መሆን የምትችሉ እንድትሆኑ እንዲሁም የስራ ክቡርነትን ተረድታችሁ እራሳችሁን ፣ ከተማችሁን እና ሃገራችሁን የምትለውጡ እንድትሆኑ ጥሪ አስተላልፋለሁ።

ትጉሀን እጆችን ከስራ ማገናኘት የሚያስችሉ በገበያው የሚፈለጉ የሞያ መስኮችን እየለየን በማሰልጠንና በመደገፍ የአምራቾችን ቁጥር እየጨመርን ከተማችንን የምትሸምት ብቻ ሳትሆን የምታመርትም ለማድረግ በትጋት መስራታችንን ቀጥለናል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿ ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.