ተቋማችንን በላቀ ሀሳብና የአጀንዳ የበላይነትን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ተቋማችንን በላቀ ሀሳብና የአጀንዳ የበላይነትን አስጠብቀን መዝለቅ ይጠበቅብናል “ወ/ሮ እናት-ዓለም መለሰ

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2017 መሪ ዕቅድ ውይይትና የ2016 በጀት ዓመት የላቀ የዕቅድ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የክፍለ ከተማ፣የወረዳ እና የሴክተር ኮሙዩኒኬሽን ዘርፎች እውቅና ተሰጠ።

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ እናትዓለም መለስ እንደተናገሩት ፡- መረጃን ከምንጩ አጥርተን በመውሰድ ብሎም ሚዛናዊ የጋዜጠኝነት የመረጃ ስርጭት መርህን ተከትለን ለህዝብ በማድረስም ጭምር፤ በምንሰጣቸው መረጃዎች በሁሉም ረገድ ለልማት ስራዎች ምቹ መደላድልን በሚፈጥር አኳሃን የሀሳብና የአጀንዳ የበላይነት መያዛችንን አጠናክረን ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት መሪ የዕቅድ እና ከፊታችን ባሉ ቀናት በከተማዋ ተግባራዊ በሚደረጉ ወሳኝ ኲነቶች ማለትም በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ፣የአፍሪካ የከተሞች ፎረምን እና በጳጉሜ ቀናት የተያዙ ዕቅዶች ከግብ ለማድረስ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ቢሮ ሀላፊዋ አሳስበዋል።

የ2016 የዕውቅናና የሽልማት መረሀ-ግብር የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ክፍለ ከተሞች ማለትም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በጥቅል የሥራ አፈጻጸማቸው የተለዩ ክፍለ ከተሞች አዲስ ከተማ፣ልደታ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ኢንዲሁም ከ11ክፍለ ከተሞች ስር ካለ ወረዳዎች ከአንደኛ እስከ ሦሰተኛ ሆነው በደረጃ የተለዩ ወረዳዎች ዕውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም ለሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮች እና ለበጎ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በዕውቅናና የሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።

በመጨረሻም በመረሀ-ግብሩ ላይ ፣በህዝብና በመንግስት መካከል ተግባቦት እንዲፈጠር ለማስቻል የላቀ ሀሳብና ተቋማዊ የአጀንዳ የበላይነትን የማስጠበቅ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ተብሏል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.