ዛሬ ማለዳ በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብራችንን በ168 የመትከያ ቦታዎች በ250 ሄክታር መሬት ላይ ጀምረናል።
የከተማችን ህዝብ ያደረግነውን ጥሪ ተቀብሎ በማለዳ በነቂስ ወጥቶ በተከላው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
ዲፕሎማቶች፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት አመራሮች ‘የጀመርነውን ሳንጨርስ አንገባም’ በሚል በችግኝ ተከላው ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ከስድስት መቶ ሚሊዮን ውስጥ ስድስት ሚሊዮኑን ችግኞች የምትተክለው አዲስ አበባ!
የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ!
እንበርታ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿ ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.