"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ "
እስካሁን ባከናወንናቸው የአረንጓዴ አሻራ መረሀ ግብሮች እንደ ከተማችንም እንደ ሀገራችንም ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግበናል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐብይ አህመድ የቀረበውን የአረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ ጥሪ ተቀብለን እንደ ሀገር 600 ሚሊዮን እንደ አዲስ አበባ ደግሞ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አሻራችንን ማሳረፍ ጀምረናል።
በጠዋቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ፒኮክ መናፈሻ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር አሻራችንን ማሳረፍ ጀምረናል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ጥሪ መሠረት አዋቂዎች ከ20 በላይ ታዳጊዎች ደግሞ ከ10 በላይ ችግኞችን በጥራት በመትከል የምናሳካው ሲሆን መንከባከቡም የሁላችንም ሀላፊነት ነው"።
አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስአበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.