የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር !
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን ተቀላቅሏል፡፡
በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሪት ፋዒዛ መሀመድ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለን ከግብ ለማድረስ ሁሉም የከተማችን ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ አረንጓዴ አሻራ እያሳረፈ ይገኛል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ዛሬና ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ ለተያዘው ሀገራዊ አረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዛሬው አንድ ጀምበር መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላናን ጨምሮ የቋሚ ኮሚቴ አመራርና ሰራተኞች የአንድ ጀንበር አሻራቸውን በየካ ጉራራ ሜዳ ላይ ተክለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.