234 ሚሊየን

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

234 ሚሊየን

"የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ" የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስከ ረፋዱ 5 ሰአት 30 ድረስ 234 ሚሊየን ችግኞች ተተክለዋል፡፡

ሰላማዊት ካሳ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሚኒስትር ዴኤታዋ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን የችግኝ ተከላ በመላ ሃገሪቱ በከፍተኛ የዜጎች ተሳትፎ እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ችግኝ ተከላ እስከ ረፋዱ 5 ሰአት ከ30 ድረስ 11 ሚሊየን ዜጎች በተከላው ተሳትፈዋል፣ 93 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ከ 2 ሺህ በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በመላው ኢትዮጵያ መሰማራታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ይህንን ሃገራዊ ሁነት በቀጥታ ስርጭት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግም ከ50 በላይ የቀጥታ ስርጭት መሳሪያዎች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.