ባለስልጣኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቅ ቆሻሻ በመኪና ጭኖ በማስገባት የጣለውን ግለሰብ መቅጣቱ አስታወቀ
ከአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ለቡ አካባቢ ከጽዳት አሰተዳደር ፍቃድ ሳይሰጠው ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ደረቆቅ ቆሻሻን ወደ ከተማዋ በተሽከርካ ጭኖ በማስገባት ባልተፈቀደ ቦታ የጣለውን ግለሰብ በገንዘብ መቅጣቱ አስታወቀ።
ግለሰቡ ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር በማዋል በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ተራ ቁጥር 31.2 መሰረት100,000/መቶ ሺህ/ ብር ተቀጥቷል
በተመሳሳይ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ1 መርካቶ አካባቢ አንድ ድርጅት ቆሻሻን በአይሱዙ መኪና ጭኖ ባልተፈቀደ ቦታ በመጣሉ በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ተራ ቁጥር 31.2 መሰረት100,000/መቶ ሺህ/ ብር የተቀጣሲሆን በዛው አካባቢ አንድ ድርጅት ባልተፈቀደ ቦታ ደረቅ ቆሻሻን በመጣል በማቆሸሹ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 ተራ ቁጥር 11 መሰረት 20,000/ሃያ ሺህ/ ብር
ተቀጥቷል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋ ውብ፣ጽዱ እና ማራኪ ለማድረግ ቀን ከሊሊት እየሰራ ሲሆን የተሠራውን ልማት እና የአካባቢ ውበቱ ሆን ብለዉ እያጠፉ ያሉትን አንዳንድ ግድ የሌሽ ግለሠቦች ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች እያጋለጡ እንዲሰጡ ባለስልጣኑ ጠይቋል።
ባለስልጣኑ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን በዛሬው ዕለት በተወሰደዉ ቅጣት መረጃውን የሰጡት የከተማዉን ነዋሪዎች አመስግኗል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.