ባለስልጣኑ መሬት የወረሩ እና ባልተፈቀደ ቦታ ሽ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ መሬት የወረሩ እና ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት የሸኑ 22 ግለሰቦች መቅጣቱ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የህዝብና የመንግስት የሆነ መሬት በህገወጥ መንገድ የወረሩ ግለሰቦች እና በከተማው ባልተፈቀደ ቦታ ሽንት የሸኑ 22 ግለሰቦች መቅጣቱ አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረደ 11 ባልታፋቃደ ቦታ ሽንታቸው ሸንተው አካባቢ ያቆሸሹ 22 ግለሰቦች በባለስልጣኑ በተሻሻለዉ የቅጣት ሰንጠረዥ 2 ደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት 22 ሰዎች እያንዳንዳቸው 2000 ሺህ ብር አጣቃላይ 44000 ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማደረጉ ገልጿል 

በተጨማሪም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የህዝብና የመንግስት የሆነ መሬት በህገወጥ መንገድ በመውረር ታጥሮ የነበረ 5 ቦታዎች በአጠቃላይ 2,200 ካሬ ሜትር መሬት በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እርምጃ መወሰዱ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በህገ ወጦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ሆን ብለዉ ደንብ የሚተላለፉ አንዳንድ ግድ የሌሽና ስግብግብ ግለሠቦች ልማት ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.